የመጀመሪያው የብሪክስ የቅዱስ ቁርኣን ውድድር በሩሲያ ካዛን ከተማ ተከፈተ

ሰብስክራይብ
የመጀመሪያው የብሪክስ የቅዱስ ቁርኣን ውድድር በሩሲያ ካዛን ከተማ ተከፈተ ዝግጅቱ በካዛን ሩሲያ ረቡዕ እለት የተከፈተ ሲሆን የብሪክስ ሀገራት፣ የነፃ ሀገራት ኮመንዌልዝ፣ እስያ እና አፍሪካን ጨምሮ ከ20 ሀገራት የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል። በውድድሩ ቁርኣን አንባቢዎች ለ"ቲሊያዋ" ሽልማት የሚፎካከሩ ሲሆን ለተቀደሱ የቁርኣን ፅሁፎች ጥበባዊ አነባበብ እውቅና እንደሚሰጥ  የሩሲያ ሙፍቲ ምክር ቤት የመጀመሪያ ምክትል ሊቀመንበር ሩሻን አቢያሶቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ ከሆነ ለትልቁ ዓለም አቀፍ የሐይማኖት ውድድር የሚሰጠው ሽልማት ምርጥ አንባቢ ተብሎ ለሚመረጠው ተወዳዳሪ ይደርሳል። "ሩሲያ በሀፊዝ (የሙስሊም ቅዱስ መፅሃፍን በልቡ የሚያውቅ ሰው) ያሲር ዶዳርቤኮቭ ትወክላለች። ዳኞቹን በሻርጃ የቅዱስ ቁርኣን አካዳሚ ሀላፊ የሆኑት ካሊፋ መስባህ አል-ቱኔጂ እንደሚመሩት" አቢያሶቭ ጨምረው ገልጸዋል። በሩሲያ ሙፍቲ ካውንስል እና በሞሀመድ ቢን ዛይድ የሂዩማኒቲስ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ይህ ውድድር የቁርኣንን መንፈሳዊ እና ሞራላዊ እሴቶች የሚያጎላ የቲያትር ዝግጅትንም ያካትታል። ሚኒስትሮች፣ ሙፍቲዎች፣ ምሁራን እና ከዓለም ዙሪያ የመጡ ዋና ዋና የሙስሊም ድርጅቶች መሪዎች በእንግድነት ይገኛሉ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0