የሐምሌ 18 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 18 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 ቭላድሚር ፑቲን ከሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሻር አል-አሳድ ጋር በሞስኮ ተገናኙ። 🟠 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ማህበር ዝግጅቶች ላይ ለመሳተፍ ላኦስ ገቡ። 🟠 11 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሲያ ኩርስክ፣ ቤልጎሮድ ክልሎች፣ ክራይሚያ እና ጥቁር ባህር በአንድ ምሽት እንደወደሙና እንደተጨናገፉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ በክረምቱ መጨረሻ 14 ሌፐርድ 2 ታንኮችን ወደ ዩክሬን እንደሚልኩ የኔዘርላንድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያ በዩክሬን በኩል ከሩሲያ የነዳጅ አቅርቦት በድጋሚ የመጀመር እቅዳቸውን እንደማይደግፉ የህብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶች አካሂደውት በነበረው ስብሰባ መግለፃቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከፕሬዝዳንታዊ ውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉት "ችቦውን ለአዲሱ ትውልድ ለማስተላለፍ" ነው ሲሉ ለአሜሪካ ህዝብ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0