ሩሲያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን አሌክሳንደር ፓንኪን በG20 የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። "ሩሲያ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ለማቅረብ፣ የውሃ ሃብቶች ያሉባቸውን ቦታዎች ማልማት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተሞክሮ ለመለዋወጥ እና የውሃ አቅርቦትን ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም ውሃን በምክንያታዊነት መጠቀም የሚቻልባቸውን መንገዶች ዙሪያ ሩሲያ ያላትን ቁርጠኝነት ታረጋግጣለች" ብለዋል።እንደ ፓንኪን ገለጻ ሞስኮ "ተመጣጣኝ የሆነ የውሃ ማጣሪያ እና በግብርና መስክ ለመስኖ የሚሆኑ ውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን እውቀት ማካፈልን ጨምሮ በአነስተኛ የውሃ ፍጆታ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ሰብሎችን ለማስተዋወቅ" ታስባለች ብለዋል። "ከመካከለኛው እስያ ጎረቤቶቻችን ጋር ተቀራርቦ የመስራት ባህል አለን። በሩሲያ የቀረበው እና የወንዞችን ንፅህና ሁኔታ ለማሻሻል የውሃ ሃብት ብክለትን ለመከላከል ያለመ የብሪክስ ንፁህ ወንዞች(BRICS Clean Rivers)ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ ነው" ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
ሩሲያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን አሌክሳንደር ፓንኪን በG20 የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።... 24.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-24T12:32+0300
2024-07-24T12:32+0300
2024-07-24T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
12:32 24.07.2024 (የተሻሻለ: 13:20 24.07.2024)
ሰብስክራይብ