ላይቤሪያ ፀረ ግብረ ሰዶም ህጓን እየከለሰች ነው።
የላይቤሪያ የተወካዮች ምክር ቤት የስርዓተ-ፆታ፣ የጤና እና የፍትህ አካላት ኮሚቴዎች የፀረ-ግብረ-ሰዶም ህግን ለማሻሻል የቀረበውን ሀሳብ እንዲያዩት ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
በተወካዩ ጆንሰን ኤስ ኤን ዊሊያምስ የቀረበው ረቂቅ ህግ ግብረ ሰዶምን ወንጀል ለማድረግ ያለመ ሲሆን እ.ኤ.አ የ1986 ህገ መንግስት ላይ የላይቤሪያን ባህል ለመጠበቅ የቀረበውን ድንጋጌ ለማክበር ነው። ረቂቅ አዋጁ በምክር ቤቱ ለውይይት ከቀረበ በኋላ ለበለጠ ግምገማ ወደ ኮሚቴው ተልኳል።
ሕጉ ላይቤሪያ በግብረሰዶማውያን ጉዳይ ላይ ያላትን አቋም በግልፅ ያሳያል ሲሉ ዊሊያም ይገልፃሉ። በላይቤሪያ የተመሳሳይ ጾታ ድርጊቶች ቀድሞውኑም ቢሆን እስከ ሦስት ዓመት እስራት ያስቀጣል።
"ሪፐብሊኩ የላይቤሪያውያንን አወንታዊ ባህል ይጠብቃል፤ ይከላከላል እንዲሁም ያስተዋውቃል፣ ከህዝባዊ እና ሀገራዊ እድገት ጋር የሚጣጣሙ ልማዳዊ እሴቶች ተቀብለው የላይቤሪያ ህብረተሰብ ፍላጎቶች ዋነኛ አካል ሆነው እንዲዳብሩ ያደርጋል" ሲል የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የረቂቅ ሕጉን ሃሳብ ጠቅሶ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ላይቤሪያ ፀረ ግብረ ሰዶም ህጓን እየከለሰች ነው።
ላይቤሪያ ፀረ ግብረ ሰዶም ህጓን እየከለሰች ነው።
Sputnik አፍሪካ
ላይቤሪያ ፀረ ግብረ ሰዶም ህጓን እየከለሰች ነው። የላይቤሪያ የተወካዮች ምክር ቤት የስርዓተ-ፆታ፣ የጤና እና የፍትህ አካላት ኮሚቴዎች የፀረ-ግብረ-ሰዶም ህግን ለማሻሻል የቀረበውን ሀሳብ እንዲያዩት ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። በተወካዩ ጆንሰን ኤስ ኤን... 22.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-22T10:43+0300
2024-07-22T10:43+0300
2024-07-22T11:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий