ሩቶ በኬንያ እየተካሄዱ ያሉ የተቃውሞ ሰልፎች መቆም አለባቸው ሲሉ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው "ፍትህ እንዲሰፍን" ጠይቀዋል

ሰብስክራይብ
ሩቶ በኬንያ እየተካሄዱ ያሉ የተቃውሞ ሰልፎች መቆም አለባቸው ሲሉ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው "ፍትህ እንዲሰፍን" ጠይቀዋል   ከውይይት በፊት ፍትህ መቅደም አለበት ሲሉ የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ተናግረው፤ በተቃውሞ ሰልፉ ወቅት " የፖሊስ ጭካኔ ሰለባዎች ሁሉ" ካሳ እንዲከፈላቸው" ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የግብር ማሻሻያያቸውን ወደ ጎን በመተው ብሄራዊ የውይይት ሀሳብ ቢያቀርቡም በመላ ሀገሪቱ ሰልፎች ቀጥለዋል። ተቃዋሚዎች በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። " እንደዚህ ያሉ ነገሮች እንደሚቆሙ ቃል መግባት እፈልጋለሁ። ይበቃል!" ሲሉ   ሩቶ ተናግረዋል። “ሀገራችንን ሊያፈርሱ ይችላሉ” ያሉትን “ዘራፊዎች” እና “ገዳዮችን” ለማስቆምም ቃል ገብተዋል። "እኛ የምንፈልገው ሰላማዊ፣ የተረጋጋች ሀገር ነው። ጉዳዮቻችንም ቢሆኑ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይፈታሉ" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0