ለአፍሪካ ደረጃ የሚሰጥ ኩባንያ በሚቀጥለው አመት ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል

ሰብስክራይብ
ለአፍሪካ ደረጃ የሚሰጥ ኩባንያ በሚቀጥለው አመት ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል ተቋሙ ራሱን የቻለ እና በአፍሪካ ሕብረት ባለቤትነት የማይመራ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት የልማት፣ የንግድ፣ የቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ በጋና አክራ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ሙቻንጋ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተነገሩት እኛ አፍሪካውያን "ከደረጃ አሰጣጥ እና ብድር ጋር በተያያዘ በሚገባ እየተመዘንንጥሩ እንዳልሆነ ይሰማናል። "የአፍሪካ የካፒታል ገበያን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ኩባንያው የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በአፍሪካውያን የተገነባ ተቋም ያስፈልገናልን፤ በዚህም አፍሪካውያን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በእኩል ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው ብድር ሊያገኙ የሚችሉበትን እድል ይፈጥራል ብለዋል። ውጥኑ በአፍሪካ ፒር ሪቪው ሜካኒዝም፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተመራ ነው። ሙቻንጋ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥ የመጨረሻውን የስራ እቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0