እንግሊዝ ህገ-ወጥ ስደትን "ከምንጩ" ለመግታት የሚውል የ84 ሚልየን ፓውንድ ፕሮጀክት ለአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ይፋ አደረገች
ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር መንግሥታቸው “ህገ-ወጥ የዝውውር አውታሮችን ለማፈራረስ ከአውሮፓ ጋር በደህንነት መረጃ እና ልምድ ልውውጥ ዙርያ እንደሚተባበር” ቃል ገብተዋል።
"ህገ-ወጥ ስደትን ለማስቆም ከምንጩ መግታት አለብን። ስለዚህ ዛሬ በአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ለሚከነወኑ ፕሮጀክቶች የ84 ሚልየን ፓውንድ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አድርጌያለሁ። ይህም የሰብዓዊ እና የጤና ድጋፍ፣ የክህሎት ስልጠና፣ የስራ እድል ፈጠራን እና የትምህርት ተደራሽነትን ያካትታል” ብለዋል አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር።
እ.አ.አ. እስከ መጋቢት 2024 ድረስ 38,546 መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እንደገቡ መንግሥት አስታውቋል።
አዲሱ የሌበር መንግሥት ከሩዋንዳ ጋር ተደርሶ የነበረውን አጨቃጫቂ የስደተኞች ስምምነት መሰረዙን ተከትሎ ኪጋሊ ቀድሞ የደረሳትን 350 ሚልየን ዶላር ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልሆነች ባለፈው ሳምንት ገልጻለች። ስምምነቱ በብሪታንያ የገንዘብ ድጋፍ ከእንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ማዘዋወር ይመለከታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
እንግሊዝ ህገ-ወጥ ስደትን "ከምንጩ" ለመግታት የሚውል የ84 ሚልየን ፓውንድ ፕሮጀክት ለአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ይፋ አደረገች
እንግሊዝ ህገ-ወጥ ስደትን "ከምንጩ" ለመግታት የሚውል የ84 ሚልየን ፓውንድ ፕሮጀክት ለአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ይፋ አደረገች
Sputnik አፍሪካ
እንግሊዝ ህገ-ወጥ ስደትን "ከምንጩ" ለመግታት የሚውል የ84 ሚልየን ፓውንድ ፕሮጀክት ለአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ይፋ አደረገች ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር መንግሥታቸው “ህገ-ወጥ የዝውውር አውታሮችን ለማፈራረስ ከአውሮፓ ጋር... 20.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-20T20:24+0300
2024-07-20T20:24+0300
2024-07-20T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
እንግሊዝ ህገ-ወጥ ስደትን "ከምንጩ" ለመግታት የሚውል የ84 ሚልየን ፓውንድ ፕሮጀክት ለአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ይፋ አደረገች
20:24 20.07.2024 (የተሻሻለ: 20:40 20.07.2024)
ሰብስክራይብ