የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬንን ግጭት ከሩሲያ ውጭ መፍታት አይቻልም አሉ

ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬንን ግጭት ከሩሲያ ውጭ መፍታት አይቻልም አሉ "ምንም አይነት የሰላም ተልዕኮ ተነሳሽነት ሁለቱንም ወገኖች ማካተት አለበት። አንድ አይነት መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ግኑኝነት እንዲኖር። በዚህ ሂደት ያለ ሩሲያ ተሳትፎ ሰላም ማሳካት የሚቻልበት መንገድ አይታየንም" ሲሉ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ በለንደን አናሊቲካል ማዕከል ንግግር ካደረጉ በኋላ አብራርተዋል። ባለስልጣኑ በለንደን ባደረጉት ጉብኝት በዩክሬን ጉዳይ ዙርያ ከብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል። "ያልተስማማንበት ነጥብ የዩክሬን እና ሩሲያን ጉዳይ ታላቋ ብሪታንያ የምታይበት መንገድ እና እኛ የግጭቱን አፈታት እንዴት እንደምንመለከተው ነው። ነገር ግን ግንኙነታችንን ለመቀጠል ተስማምተናል" ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ሚኒስትር አፅንዖት ሰጥተዋል። እ.አ.አ ሰኔ 2023 የሰባት አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ኪዬቭ እና ሴንት ፒተርስበርግን ጎብኝተው የሁለቱን ወገን ግጭት ለማርገብ፣ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ማካሄድ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር መሰረት የሀገራትን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ፣ እስረኛ መለዋወጥ፣ የድህረ ጦርነት ግንባታ እና ሌሎች ሃሳቦችን ያካተተ ባለ 10 ነጥብ የሰላም ተነሳሽነት አቅርበዋል። ለእነዚህ አንዳንድ ነጥቦች ምላሽ የሰጡት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምንም እንኳን የሰላም ስምምነት በኢስታንቡል ቢጀመርም ዩክሬን ከድርድሩ ራሷን እንዳገለለች ገልጸው ይህንንም ለአፍሪካ መሪዎች አሳይተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0