"ዓለም ያለ አፍሪካ ወደፊት መጓዝ አትችልም" ሲል ሴኔጋላዊው ጸሃፊ እና ስራ ፈጣሪ ኒዳዬ ቦካር ኒያንግ ተናገረ

ሰብስክራይብ
"ዓለም ያለ አፍሪካ ወደፊት መጓዝ አትችልም" ሲል ሴኔጋላዊው ጸሃፊ እና ስራ ፈጣሪ ኒዳዬ ቦካር ኒያንግ ተናገረ በዚህም "በሌሎች ዘንድ እየተጥላላ የሚገኘው ስደት እንዲቆም ዓለም አፍሪካውያን ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን እና ትምህርታቸውን ማስመለስ እንዲችሉ መርዳቱ ተጠቃሚ ያደርገዋል" ሲል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ጸሃፊው አፍሪካ "ለተሻለ መጪ ዓለም ቀዳሚ ሚና መጫወቷን መቀጠል አለባት" ሲል አሳስቧል። "ዜግነታችንን፣ መሪነታችንን፣ በራስ መተማመናችንን በትምህርት ነው የምናገኘው" ሲልም ስራ ፈጣሪው አክሎ ገልጿል። ጥሩ ትምህርት "አርአያ የሚሆኑ ሴኔጋል ወይም አፍሪካዊ ተብለው ሊጠሩ የሚገባቸው" "የነገዋን አፍሪካ የሚገነቡ" ሰዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የኒዳዬ ቦካር ኒያንግ መጽሐፍ "The French School, a Weapon of Mass Deconstruction," መንግሥታት የትምህርት አሰራራቸውን እንዲገመግሙ ፕሮፌሰሮች እና አስተማሪዎች በበኩላቸው እራሳቸውን እንዲያሻሽሉ ይጠይቃል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0