ማሊ በሶቪየት ህብረት ስፔሻሊስቶች በተገነባ ፋብሪካ ውስጥ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን መጠገኛ እና መገጣጠሚያ ወርክሾፕ ልትከፍት ነው

ሰብስክራይብ
ማሊ በሶቪየት ህብረት ስፔሻሊስቶች በተገነባ ፋብሪካ ውስጥ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን መጠገኛ እና መገጣጠሚያ ወርክሾፕ ልትከፍት ነው የማሊ መከላከያ ሃይል በአሁኑ ወቅት በርካታ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን እንደሚጠቀምና በማርካላ የተከፈተው አዲሱ ማእከል "በመሬት ላይ ካሉ እውነታዎች ጋር እንዲላመዱ" ያስችላቸዋል ሲሉ የማሊ የሽግግር ምክር ቤት የመከላከያ እና ደህንነተ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ ፎሴይኖ ኡታራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ "ማሊያውያን ከሩሲያ በሚመጡ መሳሪያዎች መስራት ቀላል ይሆንላቸዋል" ብለዋል፡፡ "እንደምታውቁት በወታደራዊ ኃይላችን ውስጥ ሩሲያ ውስጥ የተማሩ እና የሰለጠኑ ብዙ ስፔሻሊስቶች አሉን፡፡ እነዚህ ስፔሻሊስቶች የሩሲያ ቴክኖሎጂ፣ የሩሲያ ቴክኒኮችን፣ የሩሲያ መሳሪያዎችን የሚያውቁ ናቸው" ሲሉ አብራርተዋል። ከፍተኛ ባለስልጣኑ እንዳሉት ቀደም ባሉት ጊዜያት በባማኮ የሚታዘዙ የጦር መሳሪያዎች "በኢኮዌስ ወደቦች ውስጥ ብዙ ጊዜ ይታገዳሉ።" "እነዚህን መሳሪያዎች በሀገራችን ማሰባሰብ ከቻልን ደስተኞች ነን። ምክንያቱም የታንኮች መገጣጠምያ ዎርክሾፕ ብቻ ሳይሆን መሳርያዎችን ለመስራት ይሆናል። ጥይቶችን እና ባሩድንም ጨምሮ" ሲሉ አስተያየታቸውን አገባደዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0