የሐምሌ 10 የረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 10 የረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 የብሪታኒያ አየር ሃይል ግሩብ ጂ120ቲፒ-ኤ ፕሪፌክት ቲ1 የማሰልጠኛ እና የአብራሪ አውሮፕላን በዩክሬን ግዛት በተለይም በካርኮቭ አቅራቢያ እንደታየ የፍላይራዳር መረጃ አሳይቷል። 🟠 ስለ አዲሱ የዩክሬን የሰላም ኮንፈረንስ አስተያየት የሰጡት የሃንጋሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፒተር ሲጃርቶ "ስኬታማ እንዲሆን ከተፈለገ” ሩሲያም በዚህ ጉባኤ መወከሏን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል። 🟠 ባይደን ከብላክ ኢንተርቴንመንት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዶክተሮች የጤና እክል እንዳለባቸው ካረጋገጡ ከፕሬዝዳንታዊ ፉክክሩ እራሳቸውን እንደሚያገሉ ተናግረዋል። 🟠 በዶናልድ ትራምፕ ላይ ያነጣጠሩ አዲስ የግድያ ሙከራዎች በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊደረጉ እንደሚችሉ ፖሊቲኮ ዘግቧል። 🟠 ኤለን መስክ የኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ዋና መስሪያ ቤትን በአካባቢው ባለስልጣናት ድርጊት ምክንያት ከካሊፎርኒያ ወደ ቴክሳስ ማዛወሩን አስታውቋል። በተጨማሪም "ወደ ህንጻው ለመግባት እና ለመውጣት የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኖችን ማምለጥ" እንደሰለቸው ተናግሯል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0