የሐምሌ 9 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሩሲያ አየር መከላከያ በሩሲያ ግዛቶች ሲበሩ የነበሩ 13 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ጀምበር አውድሟል። በቤልጎሮድ ክልል ከጠላት በተተኮሶ ጥይት አራት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል።
የሪፐብሊካኑ ብሄራዊ ኮንቬንሽን ትራምፕን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት የፓርቲው እጩ ተወዳደሪ አድረጎ መርጧል። ትራምፕ ሴኔተር ቫንስን ምክትል ፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪያቸው አድርገው መምረጣቸውን አስታውቀዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብተዋል።
አሜሪካዊው ቢሊየነር ኢሎን መስክ የትራምፕን የፕሬዝዳንትነት ዘመቻ ለሚደግፈው አዲስ የፖለቲካ ኮሚቴ በወር 45 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጥ ማቀዱን ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።
ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት በመተቸታቸው ሳቢያ በሕንድ የዩክሬን አምባሳደር ወደ ሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ለማብራሪያ መጠራታቸውን ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የባንዲዶስ የሞተር ሳይክል ክለብ አባላት ለዩክሬን ታጣቂ ሃይል እየተዋጉ መሆናቸውን በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ውስጥ ያለ አንድ ምንጭ ተናገረ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሐምሌ 9 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሐምሌ 9 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሐምሌ 9 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች የሩሲያ አየር መከላከያ በሩሲያ ግዛቶች ሲበሩ የነበሩ 13 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ጀምበር አውድሟል። በቤልጎሮድ ክልል ከጠላት በተተኮሶ ጥይት አራት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል። የሪፐብሊካኑ... 16.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-16T11:54+0300
2024-07-16T11:54+0300
2024-07-16T12:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий