በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች
▪ ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የትራምፕ ረዳቶች ተናግረዋል።
▪ የህግ አስከባሪ ባለስልጣናት በትራምፕ የግድያ ሙከራ ዙሪያ ለባይደን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
▪ ባይደን በፔንስልቬንያ በተደረገው የትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ወቅት የነበረውን የደህንነት እርምጃዎችን በሙሉ እንዲገመገም ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
▪ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮችን ጠቅሰው እንደተናገሩት የግድያ ሙከራ ያደረገው ግለሰብ ከአክራሪ ድርጅቶች አልያም "ትልቅ ሴራ" ስለመኖሩ የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ገልጸዋል።
▪ ተኳሹ የተጠቀመበት ሽጉጥ አባቱ በህጋዊ መንገድ የገዛው እንደሆነ ተገልጿል።
▪ ተጠርጣሪው ቶማስ ማቲው ክሩክስ በትምህርት ቤት ውስጥ " ዝምተኛ ልጅ" እንደነበር እና ብዙ ጓደኞች ያልነበሩት እንደነበር ተገልጿል።
▪ የ20 አመቱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ሪፐብሊካን እንደነበረ የፔንስልቬንያ የመራጮች መዛግብት አመላክቷል።
▪ በተጠርጣሪው ቤት እና መኪና ውስጥ ፈንጂ የሚሠሩ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል።
▪ የአካባቢው ፖሊሶች እና የአይን እማኞች ከድጋፍ ሠልፉ በፊት ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ላይ አጠራጣሪ ባህሪ ተመልክተው መረጃውን ለደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች ሪፖርት አድርገው ነበር።
▪ የፔንስልቬንያ የድጋፍ ሰልፍ ታዳሚዎች የግድያ ሙከራው እንዲፈጸም የፈቀዱት የደህንነት አባላት ባሳዩት “የደህንነት ሥነ ምግባር መጣስ” አስደንግጧቸዋል።
▪ ተጠርጣሪው የተኮሰበት ጣሪያ የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅቱ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ፍተሻ ተደርጎ እንደነበር ተገልጿል።
▪ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የሪፐብሊካን አባል የሀገሪቱን የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ የትራምፕን ደህንነት ለማስጠበቅ ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ከሰዋል።
▪ የትራምፕ የደህንነት ጥበቃ እንዲጨምር የቀረበለት ጥያቄ መኖሩን የአሜሪካው ደህንነት አገልግሎት ውድቅ አድርጓል።
▪ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ሰራተኞች እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ እና ዌስት ፓልም ቢች ያሉ ቢሮዎችን እንዳይሄዱ ተነግሯቸዋል፤ ምክንያቱም የደህንነት ፍተሻዎች መደረግ ስላለበት እንደሆነ ተነግሯል።
▪ እ.አ.አ ከሐምሌ15-18 የሚካሄደው የሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽን የጸጥታ እቅድ እየተከለሰ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች
በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች
Sputnik አፍሪካ
በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች ▪ ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የትራምፕ ረዳቶች ተናግረዋል። ▪ የህግ አስከባሪ ባለስልጣናት በትራምፕ የግድያ... 15.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-15T12:38+0300
2024-07-15T12:38+0300
2024-07-15T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች
12:38 15.07.2024 (የተሻሻለ: 13:20 15.07.2024)
ሰብስክራይብ