የሐምሌ 8 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
በአንድ ምሽት 22 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወድመዋል። ከዚህም ውስጥ 15 በብራያንስክ ክልል፣ 6 በክራይሚያ እና አንድ በሊፕስክ ክልል ላይ መውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዩክሬን ወታደሮች ሰላማዊ የህዝብ መኖሪያ አካባቢዎችን መምታታቸውን ቀጥለዋል። ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በኬርሰን ክልል በዲኔፐር ወንዝ በስተግራ በሚገኙ ዘጠኝ ሰፈሮች ላይ 44 ያህል የመድፍ ጥቃት መፈጸሙን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
ዶናልድ ትራምፕ እ.አ.አ ሐምሌ 13 በፔንስልቪኒያ የግድያ ሙከራ ያደረገባቸውን ግለሰብን፤ በአንድ ጥይት ያስወገደውን የደህንነት አገልግሎት ሠራተኛ 'አስደናቂ ' ብለውታል። የሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽን አ.እ.አ ሐምሌ 15 በሚልዋኪ ይጀመራል፤ ትራምፕ የፓርቲው የፕሬዚዳንታዊ እጩ ሆነው በይፋ የሚታወቁበት ቀን ይሆናል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለህዝባቸው ንግግር አድርገዋል። ይህ የሆነው በመጪው ምርጫ ዋና ተቀናቃኛቸው የሆኑት የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ ከ24 ሰዓታት በኋላ ነው።
የአውሮፓ ህብረት በነሀሴ ወር መጨረሻ በቡዳፔስት ሃንጋሪ ሊካሄድ በታቀደው መደበኛ ያልሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ትይዩ የመሪዎች ጉባኤ ለማዘጋጀት አቅዷል። የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በሩሲያ እና በቻይና ጉብኝት ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ በስብሰባው ላትሳተፍ እንደምትችል ፖሊቲኮ የብራሰልስ ምንጮችን ጠቅሶ ጽፏል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር በስፔን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሐምሌ 8 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሐምሌ 8 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሐምሌ 8 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች በአንድ ምሽት 22 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወድመዋል። ከዚህም ውስጥ 15 በብራያንስክ ክልል፣ 6 በክራይሚያ እና አንድ በሊፕስክ ክልል ላይ መውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የዩክሬን... 15.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-15T12:57+0300
2024-07-15T12:57+0300
2024-07-15T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий