በሶማሊያ እስር ቤት በተሰማ ተኩስ እና ፍንዳታ ሳቢያ በትንሹ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

ሰብስክራይብ
በሶማሊያ እስር ቤት በተሰማ ተኩስ እና ፍንዳታ ሳቢያ በትንሹ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ እስር ቤት የሚገኙ ታራሚዎች የጦር መሳሪያ ማግኘት ከቻሉ በኋላ ተኩስ እና ፍንዳታ መከሰቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የዓይን እማኞችን እና ባለስልጣናትን ጠቅሰው ቅዳሜ ዕለት ዘግበዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው ማለዳ አካባቢ በማእከላዊ ማረሚያ ቤት ውስጥ መሆኑን መገናኛ ብዙሀኑ ገልጸው፤ግርግሩ ከማእከላዊ እስር ቤት ተነስቶ ቀስ በቀስ ወደ ተቋሙ ዋና ክፍል ተዛምቷል። በአሁኑ ወቅት ሁኔታው ​​​​እንደቀጠለ ሲሆን፣ባለስልጣናት ሁኔታውን ለመቆጣጠር በሂደት ላይ መሆናቸውን የመገናኛ ብዙሃኑ አክለው ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0