የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ለሁለት ሳምንታት ያካሄደው ዘመቻ ማብቃቱን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ለሁለት ሳምንታት ያካሄደው ዘመቻ ማብቃቱን አስታወቀ "ወታደሮቻችን በአካባቢው ተልእኳቸውን ሲያጠናቅቁ በሸጃያ [ወረዳ] ስምንት የአሸባሪ ዋሻዎችን አውድመዋል" ያለው የእስራኤል ጦር በዋሻው ውስጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ላፕቶፖች እና የመገናኛ መሳሪያዎች መገኘታቸውን አስታውቋል። እስራኤል የፍልስጤም እንቅስቃሴ ሃማስ አካባቢውን ለመቆጣጠር ሙከራ ሊያደርግ ነው የሚል መረጃ ከደረሳት በኋላ ነው በሰኔ ወር መጨረሻ የምድር ጦር ወደ አካባቢው የላከችው። የመጨረሻውን ግፊት ከማድረጓ ሰዓታት በፊት የእስራኤል መከላከያ ሀይል በሰርጡ ዋና ከተማ የተጠለሉ ፍልስጤማውያን በጦርነት ከታመሰው ከተማ በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አዟል። በእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት በጋዛ ሰርጥ ከ38,243 በላይ ፍልስጤማውያን እንደተገደሉና ከ87,900 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0