የሐምሌ 04 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 04 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ዚምባብዌ በአሜሪካ ዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት ለማቆም እና የራሷን መገበያያ አጠቃቀም ለማሳደግ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለባት ሲሉ የተናገሩት የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ኒክ ማንጉዋና ከዶላር አጠቃቀም መውጣት በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት በአንድ ኦፔዴ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት ገልጸዋል። 🟠 ዩጋንዳ በተባበሩት መንግሥታት የኤክስፐርቶች ሪፖርት በምስራቅ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ የሚገኙትን ኤም23 አማፂያን ትደግፋለች መባሉን ውድቅ እንደምታደርግ የዩጋንዳ ጦር ምክትል ቃል አቀባይ ተናገሩ። 🟠 ኔቶ በአፍሪካ ሀገራት እና በመካከለኛው ምስራቅ መስፋፋቱን ይቀጥላል ሲል የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ የመጨረሻ መግለጫ አመልክቷል። 🟠 እንደ መግለጫው ከሆነ ኔቶ በ2025 ለዩክሬን 40 ቢሊዮን ዩሮ ወታደራዊ ዕርዳታ የሚመድብ ሲሆን በጥቁር ባህር እና በምስራቅ የባልካን ሀገሮች መስፋፋቱን ይቀጥላል። 🟠 የአሜሪካ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎች በጀርመን የሚሰማሩ ከሆነ ሩሲያ ወታደራዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራያብኮቭ ተናግረዋል። 🟠 ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ከኔቶ አጋሮች ጋር የመረጃ ልውውጥን ሊቀንሱ እንደሚችሉ የምዕራባውያን ሚዲያዎች ዘግበዋል። 🟠 የሩሲያ ሮስቴክ የመንግሥት ኮርፖሬሽን ወሳኝ ነገሮችን ከፈንጅ ፍንጣሪ፣ ጥይት እና ከኤፍ.ፒ.ቪ-ድሮን ጥቃቶች የሚጠብቁ አዲስ የብረት መከላከያዎችን ሞክሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0