የሊዮ ቶልስቶይ ዓለም አቀፍ የሰላም ሽልማት በሩሲያ ተጀመረ

ሰብስክራይብ
የሊዮ ቶልስቶይ ዓለም አቀፍ የሰላም ሽልማት በሩሲያ ተጀመረ በሩሲያ ታሪካዊ ማህበር፣ በሩሲያ ሰላም ፋውንዴሽን እና በሩሲያ ጦር ታሪካዊ ማህበር የሚዘጋጀው ሽልማት የሶስተኛውን የዓለም ጦርነት እና የኒውክሌርን ጥፋት ለመከላከል በተደረጉ ተግባራት የላቀ ስራ ለሰሩ የሚሰጥ ነው። ለዓለም አቀፍ ደህንነት፣ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድምን በማስቆም፣ የባለ ብዙ ዋልታ እና ሰላማዊ ዓለም ግንባታ ዙርያ ለተደረጉ ትልቅ አስተዋፅዖዎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን አካባቢዎችን ከወታደር ነፃ በማድረግ፣ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነቶችን ሰብዓዊ በማድረግ ረገድ ለተገኙ ወሳኝ ስኬቶችም እውቅና ይሰጣል። ሽልማቱ ለግለሰቦች እንዲሁም ለድርጅቶች እና እንቅስቃሴዎች ሊሰጥ ይችላል። ተላሚዎቹ በእውቅ ግለሰቦች በሚዋቀረው ዓለም አቀፍ ዳኝነት ይመረጣሉ። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ በታዋቂው ፀሐፊ ሊዮ ቶልስቶይ የልደት ቀን በአውሮፓውያኑ መስከረም 9 ሞስኮ ውስጥ ይካሄዳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0