'እውነተኛ ወዳጅ'፦ ሩሲያ እንደ ምዕራቡ ዓለም ፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎችን አታስፋፋም ሲሉ ባለሙያ ተናገሩ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸው በሞስኮ ያደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት የህንድ እና ሩሲያ ግንኙነት ዘላቂ ጥንካሬን አጉልቶ ያሳያል ሲሉ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የገለፁት የቀድሞው የህንድ ጦር ሌተናንት ኮሎኔል ጄ.ኤስ. ሶዲ ኒው ዴሊሂ በሞስኮ ተአማኒ እና መመኪያ አጋር እንዳገኘች ተናግረዋል።
"ሩሲያ እና የቀድሞው ዩ.ኤስ.ኤስ.አር መሬታቸውን ከአሜሪካ እና ከምዕራቡ ዓለም በተቃራኒ ለፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎች እንዲውል ፈቅደው አያውቁም" ብለዋል ሶዲ። "ህንድ በጭፍን የምታምናት እና የምትተማመንባት ሀገር ካለች ሩሲያ ብቻ ነች።"
በተጨማሪም ሩሲያ ለህንድ የመከላከያ ስርዓት አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎችን በተከታታይ እንደምትሰጥ ጠቁመው ይህም በምዕራባውያን በኩል የማይታይ ቁርጠኝነት እንደሆነ አንስተዋል።
ከመከላከያ ባለፈ የህንድ-ሩሲያ አጋርነት ለአካባቢው መረጋጋት ወሳኝ ነው።
"ጠንካራ እና የተቀራረበ የህንድ-ሩሲያ ወዳጅነት በቻይና፣ ፓኪስታን እና ህንድ መካከል በየጊዜው እየጨመረ ያለውን ውጥረት ለመቀነስ ይረዳል" ሲሉ ሶዲ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
'እውነተኛ ወዳጅ'፦ ሩሲያ እንደ ምዕራቡ ዓለም ፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎችን አታስፋፋም ሲሉ ባለሙያ ተናገሩ
'እውነተኛ ወዳጅ'፦ ሩሲያ እንደ ምዕራቡ ዓለም ፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎችን አታስፋፋም ሲሉ ባለሙያ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
'እውነተኛ ወዳጅ'፦ ሩሲያ እነደ ምዕራቡ ዓለም ፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎችን አታስፋፋም ሲሉ ባለሙያ ተናገሩ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሶስተኛ የስልጣን ዘመናቸው በሞስኮ ያደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት የህንድ እና ሩሲያ ግንኙነት ዘላቂ... 10.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-10T12:52+0300
2024-07-10T12:52+0300
2024-07-10T14:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
'እውነተኛ ወዳጅ'፦ ሩሲያ እንደ ምዕራቡ ዓለም ፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎችን አታስፋፋም ሲሉ ባለሙያ ተናገሩ
12:52 10.07.2024 (የተሻሻለ: 14:20 10.07.2024)
ሰብስክራይብ