የሐምሌ 3 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 3 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 ቭላድሚር ፑቲን እና ናሬንድራ ሞዲ በክሬምሊን ተወያይተዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ መሪዎቹ በዓለም አቀፍ ሁኔታ እና በብሪክስ፣ በሻንጋይ የትብብር ድርጅት እና ቡድን 20 ውስጥ ስላላቸው ትብብር መወያየታቸውን ገልፀዋል። 🟠 የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚንስትር ኦርባን በዩክሬን ያለው ግጭት በአውሮፓ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ተፅእኖ በማንሳት በሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት እንዳስረዱ ዲፒኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ዶናልድ ትራምፕን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የፖሊቲኮ ጋዜጣ የህዝብ አስተያየት ውጤት አመልክቷል። 🟠 የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ሾልስ የባይደን ሁኔታ እንደማያሳስባቸው ከኔቶ ጉባኤ በፊት ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ለህብረቱ መሪዎች ስብሰባ ዝግጁ እንደሆኑ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል። 🟠 የሩሲያ ጦር በክራይሚያ ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጀ የነበረውን ሂማርስ ኤም.ኤል.አር.ኤስ (HIMARS MLRS) ሮኬት ማስወንጨፊያ እና የዩክሬን ጦር እዝ መሰብሰቢያ ቦታን እንደደበደበ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የጥቃቱ ግብ የተሳካ ሲሆን አራት ኤም.ኤል.አር.ኤስ ማስወንጨፊያዎች ሲወድሙ መሳርያውን የሚጠግኑ 35 የሚደርሱ የውጭ ስፔሻሊስቶች መወገዳቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0