ጀርመን በኒጀር የሚገኘውን የአየር ኃይል ጦር ሰፈሯን ልትዘጋ ነው።

ሰብስክራይብ
ጀርመን በኒጀር የሚገኘውን የአየር ኃይል ጦር ሰፈሯን ልትዘጋ ነው። ቡንደስዌህር (የጀርመን ጦር ሃይሎች) በኒጀር የሚገኘውን የአየር ኃይል ጦር ሰፈር እ.አ.አ ነሀሴ 31 ልትዘጋ መሆኑን የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ወታደራዊ መኮንኖቹ ወደ ጀርመን ይመለሳሉ ተብሏል። "በኒጀር የተላለፈልን ረቂቅ ስምምነት ባህሪውም ሆነ ይዘቱ ከግምት ውስጥ በማስገባት ስምምነት ላይ ለመድረስ መሰረት ሊሆን አይችልም"ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ለጀርመን ወታደሮች የህግ ከለላ መስጠት እንደማይችሉ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩን ተናግረዋል።ስለዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ውይይቶች ቆመዋል።እናም ከአሁን ወዲያ ጀርመን በመከላከያ ሆነ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች አማካኝነት በሚኖሩ በጋራ ፕሮጀክቶች ወይም የስልጠና መርሃ ግብሮች ላይ ከሀገሪቱ ጋር አትሠራም። በኒያሚ የሚገኘው የጀርመን አየር ኃይል ጦር ሰፈር እ.አ.አ ከ2013 ጀምሮ በማሊ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ(MINUSMA) የሎጂስቲክስ ማዕከል ሆኖ አገልግሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0