ሴኔጋል ከሳዑዲ አረቢያ ኩባንያ ጋር ያላትን የውሃ ፕሮጀክት ስምምነትን እንደምትሰርዝ የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።

ሰብስክራይብ
ሴኔጋል ከሳዑዲ አረቢያ ኩባንያ ጋር ያላትን የውሃ ፕሮጀክት ስምምነትን እንደምትሰርዝ የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በ700 ሚሊዮን ዩሮ የሚፈጀው የጨዋማ ውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክት በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ትልቅ የግል ኢንቨስትመንቶች አንዱ ነው ተብሎ የተነገረለት ሲሆን በሳውዲ አረቢያ አክዋ ፓወር እና በሴኔጋል መንግስት የውሃ ኩባንያ (ሶኒስ)SONES መካከል ፤በማኪ ሳል የፕሬዚዳንትነት የመጨረሻ ቀናት የተፈረመ ሥምምነት ነው። በዳካር አቅራቢያ የሚገኘው ፋብሪካ ለዋና ከተማው እና ለሌሎች ክልሎች 400,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለማቅረብ ያለመ ነበር። "ይህ ፕሮጀክት ከመንግስት የስትራቴጂ አማራጮች ጋር አይጣጣምም፤ልንተወው ወስነናል" ሲሉ የሀገሪቱ የውሃ ሚኒስትር ቼክ ቲዲያን ዲዬ ለኤኤፍፒ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። አክለውም "በሦስት ወይም በአራት ዓመታት ውስጥ የዳካር ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በቀን ከ 400,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በላይ ያስፈልገናል ብለዋል" በተጨማሪም የመንግስት ጠበቆች ውሉን ማፍረስ ሊያስከትል የሚችለውን የህግ መዘዝ እያጠኑ ቢሆንም "የፋብሪካው ግንባታ ገና ስላልተጀመረ በሳውዲው ኩባንያ አክዋ ላይ ምንም አይነት የገንዘብ ጉዳት ሊኖር አይችልም" ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0