ናይጄሪያ አዲስ የተቋቋመው የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች።

ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ አዲስ የተቋቋመው የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የአፍሪካ ነዳጅ አምራቾች ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ኢ-መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። "የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ በመላው አፍሪካ የሚገኙ የሃይል ፕሮጀክቶችን በገንዘብ በመደገፍ እንዲሁም ፈጠራን እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስተዋወቅ ትልቅ መሠረት ይሆናል ተብሏል።የበለጸገ የኃይል ሀብታችንን ለመጠቀም እና ለማዳበር የምናደርገውን የጋራ ጥረት ያሳያል።ይህ ለናይጄሪያ እና ለመላው የአፍሪካ አህጉር አስደናቂ ድል ሲሉ የናይጄሪያ የነዳጅ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ሄኒከን ሎክፖቢሪ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። በዚህ ዓመት መገባደጃ ላይ በሚጀመረው የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ ማቋቋሚያ በጀት 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይጠበቃል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0