“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት
የዕድገት ስኬት ታሪኮች ከአፍሪካ የሚነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ "አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት" ሆና ተለይታ ትወጣላች፤ ሀገሪቱ ወደ ብሪክስ ቡድን መቀላቀሏም ዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ አጋርነቷን የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር የፊስካል ፖሊሲና የመንግስት ፋይናንስ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ ቶሊና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ ይዛ የምትመጣው የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት እድል እንዲሁም ከአባልነቷ የምታገኘው ጥቅም በጣም ከፍተኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ይህ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስፋትና አቅም የሚያሳይ ጉልህ ምልክት ነው ብለን እናምናለን። እስካሁን ያሳካነውን እና በአጠቃላይ ልናሳካው ለምንችለው ነገር ማስረጃ ነው። ስለዚህ በብሪክስ ስብስብ ውስጥ በንቃት እየተሳተፍን እንገኛለን" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከበርካታ የዓለም ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት እና የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ህብረት አባል መሆኗንም አክለዋል። ይህ ታሪካዊ መሰረት እና አሁን ያለው አቅም ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ለምትጫወተው ሚና በጥሩ አቋም ላይ እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት
“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት
Sputnik አፍሪካ
“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት የዕድገት ስኬት ታሪኮች ከአፍሪካ የሚነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ "አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት" ሆና ተለይታ ትወጣላች፤ ሀገሪቱ ወደ ብሪክስ... 04.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-04T16:43+0300
2024-07-04T16:43+0300
2024-07-04T17:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት
16:43 04.07.2024 (የተሻሻለ: 17:20 04.07.2024)
ሰብስክራይብ