የሰኔ 27 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
🟠 ኤም23 አማፂ ቡድን ህዝብ የሚበዛበትን የካሴሴን ቦታ ለመያዝ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ሰሜን ኪቩ ግዛት) ቁልፍ ወደ ሆነችው ቡቴምቦ ከተማ ለመገስገስ የሚያደርገውን ሙከራ ቀጥሏል ሲል የኮንጎ የዜና ፖርታል አክቱዋሊት ዘግቧል።
🟠 የኒጀር ባለስልጣናት ከቤኒን መንግስት ጋር ግንኙነቱን ወደነበረበት ለመመለስ እና የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለማስጀመር ድርድር ለማድረግ ተስማምተዋል።
🟠 ኬንያ የማዕከላዊ ባንክ የምጣኔ ሀብት ባለሙያውን ራፋኤል ኦዊኖን የዕዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርጋ መሾሟን የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሹመቱ ከፍተኛ የህዝብ ዕዳን ለማስተዳደር በቀረበው የታክስ ጭማሪ ላይ ተቃውሞ በተነሳበት ወቅት የመጣ ነው፡፡
🟠 በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራው የኤምኬ ፓርቲ ግንቦት 21 ተካሂዶ የነበረው ምርጫ የተጭበረበረ ነው በሚል ያቀረበውን ክስ አቋርጧል።
🟠 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አስታና በሚገኘው የነፃነት ቤተ መንግስት ደረሱ።
🟠 የአየር መከላከያዎች በብራያንስክ፣ ቤልጎሮድ እና ታምቦቭ ክልሎች ላይ አራት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እንዳወደሙ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዲሞክራቲክ ገዥዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ካደረጉት ክርክር በኋላ የህክምና ምርመራ ማድረጋቸውን እና ጥሩ ስሜት ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን ፖለቲኮ አስነብቧል።
🟠 እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደተቃረቡ ሲኤንኤን የእስራኤልን ምንጩን ጠቅሶ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰኔ 27 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
የሰኔ 27 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 27 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ኤም23 አማፂ ቡድን ህዝብ የሚበዛበትን የካሴሴን ቦታ ለመያዝ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ሰሜን ኪቩ ግዛት) ቁልፍ ወደ ሆነችው ቡቴምቦ ከተማ ለመገስገስ የሚያደርገውን ሙከራ ቀጥሏል ሲል... 04.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-04T12:56+0300
2024-07-04T12:56+0300
2024-07-04T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий