የባይደን የአእምሮ ጤና ማሽቆልቆል ሚስጥራዊ እንዳልሆነ ያልተሳካው ክርክር አሳይቷል

ሰብስክራይብ
የባይደን የአእምሮ ጤና ማሽቆልቆል ሚስጥራዊ እንዳልሆነ ያልተሳካው ክርክር አሳይቷል ከቅርብ ወራት በፊት እስከ ክርክሩ መዳረሻ ድረስ ከባይደን ጋር የሰሩ የአሜሪካ ባለስልጣናት ግራ መጋባታቸውን፣ መድከማቸውንና ከመጋረጃ ጀርባ በሚደረጉ ንግግሮች ፍሬ ነገራቸውን ሲያጡ አስተውለዋል ሲል ዘገባው ገልጿል። በቅርቡ ጣልያን ውስጥ ተካሂዶ በነበረው የቡድን ሰባት ስብሰባ የባይደን አቋም እንደተንኮታኮተ መታዘባቸውን አንድ ከፍተኛ የአውሮፓ ባለስልጣን ተናግረዋል ያለው ዘገባው አውሮፓውያኑ “ግራ የተጋባ” እና ለማነጋገር አስቸጋሪ የሆነውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሲያዩ ተደናግጠዋል ሲል አክሏል። እንደ ባለስልጣኑ ገለፃ በስብሰባው ወቅት የአውሮፓ መሪዎች ስለ ባይደን አካላዊ ሁኔታ በሚስጢር እየተወያዩ እና ፕሬዝዳንቱን ላለማሳጣት ካጠገባቸው በዝግታ ይራመዱ ነበር ብለዋል። በተጨማሪም ባይደን ባልተረጋጉበት እና ካሜራዎች ባሉበት ቅጽበት በፕሬዝዳንቱ ዙርያ እርስ በርስ በመናበብ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡ ባይደን እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው መገመት ይችሉ እንደሆነ የተጠየቁት አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣን “እኔ አላውቅም” ብለዋል። አንድ የቀድሞ የአውሮፓ ባለስልጣን ለጥያቄው “አይሆንም” የሚል ምለሽ ሰጥተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0