ባይደን እና ራማፎሳ በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያለዎት እንዳሉ እና በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ ውይይት እንዳደረጉ ኋይት ሀውስ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
“በዩኤስ እና ደቡብ አፍሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የወደፊት አጋርነት ጉዳዮች እንዲሁም የቡድን 20 አመራርነት በተመለከተ ተወያይተዋል" ሲል ኋይት ሀውስ አክሏል።
ባይደን እና ራማፎሳ እያደገ ያለውን የኢኮኖሚ ብልጽግናን ጨምሮ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ ማረጋጋጣቸውን መግለጫው ገልጿል።
በግንቦት ወር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ እና ቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ ዩናይትድ ስቴትስ ስጋቷን በሀገሪቱ ከሚካሄደው ምርጫ በኋላ እንደምትገልፅ ለኮንግረስ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
በተጨማሪም የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ከስድስት የዩኬ፣ ቻይና፣ ዩኤኢ እና ደቡብ አፍሪካ ኮርፖሬሽኖች ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ገድቧል። መቀመጫውን በዩኬ ያደረገው ሊቪንግስተን ኤሮስፔስ ከ2023 ጀምሮ በአሜሪካ ማዕቀብ ውስጥ ከነበረው የደቡብ አፍሪካ የሙከራ በረራ አካዳሚ ጋር ባለው ግንኙነት ማዕቀብ ተጥሎበታል። እነዚህ ኩባንያዎች የቻይና ወታደሮችን በአሜሪካ እና በኔቶ ቴክኖሎጂ በማሰልጠን ይከሰሳሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ባይደን እና ራማፎሳ በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ
ባይደን እና ራማፎሳ በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
ባይደን እና ራማፎሳ በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያለዎት እንዳሉ እና በወደፊት የትብብር መስኮች... 03.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-03T12:50+0300
2024-07-03T12:50+0300
2024-07-03T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ባይደን እና ራማፎሳ በወደፊት የትብብር መስኮች ዙርያ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ አስታወቀ
12:50 03.07.2024 (የተሻሻለ: 13:20 03.07.2024)
ሰብስክራይብ