የሰኔ 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የሰኔ 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ሩሲያ ከ2019 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በወጡ አልማዞች ዋጋ ቦትስዋናን በልጣ መሪ ሆነች። 🟠 ሴራሊዮን ያለ እድሜ ጋብቻን በይፋ ከለከለች። ፕሬዝደንት ጁሊየስ ባዮ አሁንም በስፋት የሚታየውን ልማድ ለማስቆም ያለመ ህግ ፈርመዋል። 🟠 የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመንግስት የማዕድን ኩባንያ ከሀገሪቱ ማዕድን ማውጫ የተገኘውን መዳብ ለመጀመሪያ ጊዜ መሸጥ ጀመረ። 🟠 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በካዛኪስታን አስታና የገቡ ሲሆን በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ተከታታይ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። 🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ በቤልጎሮድ፣ ብራያንስክ እና ሞስኮ ክልሎች ግዛቶች ላይ 10 ድሮኖችን አወደመ። በተጨማሪም ወደ ኖቮሮሲስክ የሚሄዱ ሁለት ሰው አልባ ጀልባዎች በጥቁር ባህር ወድመዋል ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዘግቧል። 🟠 የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ያቀረቡት የተኩስ አቁም ሀሳብ በዘለንስኪ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ ተናግረዋል። ኦርባን ከስዊስ ሳምንታዊ መፅሄት ዲ ዌልትዎቼ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከኪዬቭ ጋር በዚህ ጉዳይ የሚደረገው ውይይት ይቀጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። 🟠 የኔቶ አባል ሀገራት በሀገሪቱ በተንሰራፋው ሙስና ምክንያት ዩክሬንን ወደ ህብረቱ እንድትቀላቀል መጋበዝ አይፈልጉም ሲል ዘ ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡ 🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት የክርክር መድረክ ለነበራቸው ደካማ አፈጻጸም በፈረንሳይ እና በጣሊያን ያደረጉትን ጉዞ በመጥቀስ ለማስረዳት ሞክረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0