"ለሀገራችን የሚጠቅም ከሆነ ከሩሲያ ጋር ኢኮኖሚ፣ ባህልዊ ፖለቲካዊ ልውውጥ ለምን አይኖረንም?"

ሰብስክራይብ
"ለሀገራችን የሚጠቅም ከሆነ ከሩሲያ ጋር ኢኮኖሚ፣ ባህልዊ ፖለቲካዊ ልውውጥ ለምን አይኖረንም?" ይህን ያሉት በኒጀር የሚገኘው የአርበኞች ግንባር ለሉዓላዊነት ድርጅት ፕሬዝዳንት ናቸው። "አንዳንዶች ሩሲያን ማጥላላት ቀጥለዋል ምክንያቱም ለእነሱ እኛ ያለ ምዕራባውያን ምንም አይደለንም። ነገር ግን ከበርካታ አጋሮቻቸን ጋር ያለ ምዕራባውያን መኖር እንደምንችል እያረጋገጥን ነው" ሲሉ ማይኩል ዞዲ የሳህል ሀገራት ጥምረት (ኤ.ኢ.ኤስ) የሉዓላዊነት ትግልን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ውይይት ላይ ተናግረዋል። እሳቸው እንደሚሉት ጉዳዩ "አንደኛውን አለቃ በሌላኛው መተካት" አይደለም ምከንያቱም "የአርበኞች ግንባር ለሉዓላዊነት የሩሲያዊም ሆነ የፈረንሣይ ደጋፊ ሳይሆን፤ የኒጀር እና የኤ.ኢ.ኤስ ደጋፊ ነው።" ፖለቲከኛው "ከምዕራባውያን ውጭ መኖር አንችልም የሚለውን ሀሳብ ለማስወገድ" እና "ጥቅማችን ከየትም ይገኝ መፈለጋችን ምንም ችግር እንደሌለው" ለማሳየት ያለሙ ጅምሮችን እንደሚቀበሉ ገልፀዋል። "ግባችን ኤ.ኢ.ኤስ ስኬታማ ሆኖ ማየት እና ኒጄርን መልሶ ለመገንባት ዝግጁ ከሆኑ እውነተኛ አጋሮቻችን ጋር አገግማ ማየት ነው" ብለው አስተያየታቸውን አገባደዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0