#አጫጭርዜና
የስፑትኒክ አትዮጵያ የሰኔ 25 ረፋድ የዓለም ዜናዎች፡-
🟠 የሩሲያ ጦር በፖልታቫ ክልል ማይርሆሮድ ከተማ ውስጥ የዩክሬን ወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
🟠 የአሜሪካ ጋዜጠኛ ተከር ካርልሰን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በተደረገው የመጀመሪያ ክርክር ባሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ከፕሬዚዳንታዊ ውድድር ሊያባሩራቸው እንደሚገባና ከውድድሩ ያነሷቸዋል ብሎ እንደሚያምን ተናገረ።
🟠 ሰሜን ኮሪያ ሃዋሶንግፎ-11Da-4.5 የተባለውን አዲስ ታክቲካል ባሊስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን የሀገር ውስጥ ብሮድካስተር ገለፀ።
🟠 ኢራን እና ሁሉም የ“አክሲስ ኦፍ ሬዚዝታንስ’ አባላት ከእስራኤል ጋር ግጭት ከተፈጠረ የሊባኖሱን የሺዓ እንቅስቃሴ ሂዝቦላህ በማንኛውም መንገድ ይደግፋሉ ሲሉ የኢራን ከፍተኛ መሪ አማካሪ ካማል ካርራዚ ተናግረዋል።
🟠 የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን እ.አ.አ 2022 የዩክሬን ቀውስ ከተባባሰ በኋላ ለመጀመርያ ግዜ ኪዬቭ እንደገቡ የፕሬስ ሴክሬቴሪያቸው በርታላን ሃቫሲ ተናግረዋል፡፡ ኦርባን “ሰላም ማስፈን ስለሚቻልበት ሁኔታ” እና በሁለትዮሽ የግንኙነት ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
#አጫጭርዜና
#አጫጭርዜና
Sputnik አፍሪካ
#አጫጭርዜና የስፑትኒክ አትዮጵያ የሰኔ 25 ረፋድ የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 የሩሲያ ጦር በፖልታቫ ክልል ማይርሆሮድ ከተማ ውስጥ የዩክሬን ወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። 🟠 የአሜሪካ ጋዜጠኛ ተከር... 02.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-02T12:24+0300
2024-07-02T12:24+0300
2024-07-02T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий