"የምርጫው ውጤት ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የፈረንሳይ ህዝብ በዩክሬን እና ሩሲያ መኻከል የሰላም ስምምነት በአፋጣኝ እንዲደረግ የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል"
በፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር አስቸኳይ የፓርላማ ምርጫ የኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ ሽንፈትን አስመልክቶ አንድ የአውሮፓ የሕግ አውጪ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ሄርቬ ጁቪን "የዩክሬንን መብቶች" እንዲሁም በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኙ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎችን የሚያከብር ስምምነት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
"ከምርጫው ትምህርት ለመቅሰም በጣም ገና ነው" ያሉት ፖለቲከኛው ይሁን እንጂ "በቀጣዮቹ ወራት ፈረንሳይን ለማስተዳደር በጣም አስቸጋሪ ይሆናል" የሚል ስጋቱን ገልጿል።
በፓሪስ ዋና አጋሮች በኩል "በሚቀጥሉት ወራት ወይም ዓመታት ፈረንሳይ የምትመራበት መንገድን በተመለከተ ስጋት" እንዳለ ተናግሯል።
አሁን ባለው ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ "ፈረንሳይ ግልጽ የሆነ አብላጫ መንግሥት መመስረት አለመቻሏ እጅግ አደገኛ ይመስላል። ፈረንሳይ በዓለም ላይ ያላትን ገፅታ በጣም ይጎዳዋል። የፈረንሳይን ሕዝብ ጥቅም በጣም የሚጎዳ መስሎ ይታየኛል” ሲል ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ፖሊሲውን በተመለከተ “ፈረንሳይ በአፍሪካ ውስጥ ከገባችበት ውድቀት፣ ፖሊሲዋ ፈረንሳይን በብዙ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን እና አጋሮቻችን ዘንድ እንድትጠላ ካደረገ በኋላ ከማንም የማትወግነውን ፈረንሳይ የሚያከብር የረጅም ግዜ የውጭ ፖሊሲ አስፈላጊ ነው" ሲል አስምሮበታል።
“ከአሜሪካ አጋሮቻችን እንዲሁም ከቅርብ ጊዜዎቹ ታላላቅ ሀገራት ህንድና ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ዘላቂ ግንኙነቷን ማስቀጠል ከሚገባት ሀገራት ጋር እንዴት መነጋገር የምትችል" ፈረንሳይን እንደሚደግፍ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
"የምርጫው ውጤት ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የፈረንሳይ ህዝብ በዩክሬን እና ሩሲያ መኻከል የሰላም ስምምነት በአፋጣኝ እንዲደረግ የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል"
"የምርጫው ውጤት ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የፈረንሳይ ህዝብ በዩክሬን እና ሩሲያ መኻከል የሰላም ስምምነት በአፋጣኝ እንዲደረግ የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል"
Sputnik አፍሪካ
"የምርጫው ውጤት ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የፈረንሳይ ህዝብ በዩክሬን እና ሩሲያ መኻከል የሰላም ስምምነት በአፋጣኝ እንዲደረግ የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል" በፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር አስቸኳይ የፓርላማ ምርጫ የኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ ሽንፈትን... 02.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-02T10:45+0300
2024-07-02T10:45+0300
2024-07-02T11:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
"የምርጫው ውጤት ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የፈረንሳይ ህዝብ በዩክሬን እና ሩሲያ መኻከል የሰላም ስምምነት በአፋጣኝ እንዲደረግ የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል"
10:45 02.07.2024 (የተሻሻለ: 11:20 02.07.2024)
ሰብስክራይብ