#አጫጭርዜና
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ምሽት ዜናዎች፡-
🟠 እስራኤል በሐምሌ ወር አጋማሽ በደቡብ ሊባኖስ ሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ልትጀምር እንደምትችል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የምዕራባውያን ዲፕሎማቶች የእስራኤል ዘመቻ በሐምሌ ወር ሶስተኛ ወይም አራተኛ ሳምንት ውስጥ ሊጀምር እንደሚችል ያምናሉ ተብሏል።
🟠 ቢልየነር ስራ ፈጣሪው ኤለን መስክ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድጋሚ ምርጫ ካሸነፉ ፅንስ ማስወረድን በፌደራል ደረጃ ያግዳሉ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ያስተላለፉትን መልእክት ተቸ።
🟠 በዳግስታን ሪፐብሊክ ሰኔ 16 በተካሄደው የሽብር ጥቃት የምዕራባውያን አሰልጣኞች እጅ እንዳለበት በክትትል መድረስ እንደሚቻል የዳግስታን ሪፐብሊክ መሪ ሰርጌይ ሜሊኮቭ ተናግረዋል።
🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሐምሌ 9-10 በሚደረጉ ክርክሮች ላይ እንደሚሳተፉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። "ሐምሌ 9 ለፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ዘላቂነት ላለው የዓለም ስርዓት የባለብዙ ወገን ትብብርን በተመለከተ ክፍት የሚኒስትሮች ክርክር ይካሄዳል። ሐምሌ 10 የፍልስጤም ጉዳይን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ሁኔታ ግልፅ የሚኒስትሮች ክርክር ይደረጋል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት መርሃግብሮች በሰርጌ ላቭሮቭ ሊቀመንበርነት ይካሄዳል” ሲል ሚኒስቴሩ አክሏል።
🟠 በመጀመሪያ ዙር የፓርላማ ምርጫ ያሸነፈው የፈረንሳይ ቀኝ ዘመም ናሽናል ራሊ ፓርቲ ከሌሎች የህግ አውጪዎች በቂ ድጋፍ ካገኘ የፓርላማው አብላጫ መቀመጫ ባይኖረውም መሪው ጆርዳን ባርዴላን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ለመሾም እንደተዘጋጀ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ሴባስቲን ቼኑ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
#አጫጭርዜና
#አጫጭርዜና
Sputnik አፍሪካ
#አጫጭርዜና የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ምሽት ዜናዎች፡- 🟠 እስራኤል በሐምሌ ወር አጋማሽ በደቡብ ሊባኖስ ሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ልትጀምር እንደምትችል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የምዕራባውያን ዲፕሎማቶች የእስራኤል ዘመቻ በሐምሌ ወር ሶስተኛ... 01.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-01T20:12+0300
2024-07-01T20:12+0300
2024-07-01T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий