ስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ረፋድ የዓለም ዜናዎን ያቀርብላችኋል፡-
🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ በብራያንስክ፣ ኩርስክ እና ቤችልጎሮድ ክልሎች 36 የዩክሬን ድሮኖችን አንዳወደመ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
🟠 ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀቶችን ጨምሮ ሁለት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን በምሥራቅ አቅጣጫ ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱን ጦር ጠቅሰው ዘግበዋል። የአጭር ርቀት ሚሳኤሉ ወደ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲወነጨፍ ሌላኛው ሚሳኤል ደግሞ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት መሸፈኑን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
🟠 ፖሊስ በፓሪስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን የስፑትኒክ ጋዜጠኛ ዘግቧል። የተቃውሞ ሰልፉ በፓሪስ ፕላስ ዴ ላ ሪፐብሊክ አደባባይ የፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር የፓርላማ ምርጫ ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ነው የተጀመረው። በተቃውሞው ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። የናሽናል ፓርቲ እና አጋር ኃይሎች በፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር የፓርላማ ምርጫ 33.4% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
🟠 የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሃካን ፊዳን በጋዛ ሰርጥ ስላለው ሁኔታ ከተጠባባቂ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ ጋር በተወያዩበት ወቅት የሊባኖስ ግጭት መባባስ ለሶሪያ እና ኢራቅ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አንስተዋል ሲሉ የቱርክ የዲፕሎማስያዊ ምንጮችን አጣቅሰው የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በፊዳን እና ባገሪ መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት እሁድ ነው የተካሄደው። ዲፕሎማቶቹ ሽብርተኝነትን መዋጋት በተመለከተ እንዲሁም በኢኮኖሚና ትራንስፖርት ዘርፍ የሁለትዮሽ ግኑኝነታቸው ዙርያ መክረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ረፋድ የዓለም ዜናዎን ያቀርብላችኋል፡-
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ረፋድ የዓለም ዜናዎን ያቀርብላችኋል፡-
Sputnik አፍሪካ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሰኔ 24 ረፋድ የዓለም ዜናዎን ያቀርብላችኋል፡- 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ በብራያንስክ፣ ኩርስክ እና ቤችልጎሮድ ክልሎች 36 የዩክሬን ድሮኖችን አንዳወደመ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀቶችን... 01.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-01T12:30+0300
2024-07-01T12:30+0300
2024-07-01T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий