አሜሪካ እና ጭፍራዎቿ "የኔቶን ስሪት በእስያ" ፈጥረዋል ስትል ሰሜን ኮሪያ ወቀሰች
የሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃፓን ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ በወሩ መጀመሪያ የሶስትዮሽ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ "የኔቶን ስሪት በእስያ" እየፈጠሩ ነው ሲል መክሰሱን የሰሜን ኮሪያ የመንግስት የዜና አገልግሎት ኬ.ሲ.ኤን.ኤ ዘግቧል።
🪖ቅዳሜ እለት ጃፓን፣ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ያሳተፈውና ፍሪደም ኤጅ የሚል ስያሜ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ በምሥራቅ ቻይና ባህር ተጠናቋል።
በየዓመቱ የሚካሄደው ልምምድ ውጥረት በነገሰበት የኮሪያ ልሳነ ምድር ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።
"የዩኤስ-ጃፓን-ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት ክልላዊ መረጋጋትን እና ደህንነትን ለማጠናከር ያለመ ትብብር እንጂ የኔቶን ስሪት በእስያ ለመፍጠር አይደለም ስትል አሜሪካ እየተናገረችው ነው፤ ነገር ግን የጠብ አጫሪ ቡድኑ ምስረታን በተመለከተ ከሚመጣው ዓለም አቀፍ ውግዘት ለማምለጥ የሚደረግ ንግግር ነው” ሲል ሚኒስቴሩ ተናግሯል።
ሦስቱ ሀገራት ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር በካምፕ ዴቪድ አካሂደውት ከነበረው ጉባኤ በኋላ ባወጡት መግለጫ በማንኛቸውም ላይ ለሚደርስ ስጋት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተስማምተዋል።
"ይህ በመሰረታዊነት የኔቶን የጋራ መከላከያ መርህ የሚያስታውስ ነው" ሲል የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
አሜሪካ እና ጭፍራዎቿ "የኔቶን ስሪት በእስያ" ፈጥረዋል ስትል ሰሜን ኮሪያ ወቀሰች
አሜሪካ እና ጭፍራዎቿ "የኔቶን ስሪት በእስያ" ፈጥረዋል ስትል ሰሜን ኮሪያ ወቀሰች
Sputnik አፍሪካ
አሜሪካ እና ጭፍራዎቿ "የኔቶን ስሪት በእስያ" ፈጥረዋል ስትል ሰሜን ኮሪያ ወቀሰች የሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃፓን ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ በወሩ መጀመሪያ የሶስትዮሽ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ "የኔቶን ስሪት በእስያ"... 01.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-01T09:49+0300
2024-07-01T09:49+0300
2024-07-01T10:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
አሜሪካ እና ጭፍራዎቿ "የኔቶን ስሪት በእስያ" ፈጥረዋል ስትል ሰሜን ኮሪያ ወቀሰች
09:49 01.07.2024 (የተሻሻለ: 10:20 01.07.2024)
ሰብስክራይብ