የሰኔ 23 ምሽት ዋና ዋና ማጠቃለያ ዜናዎች
🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሞስኮ እና በሚንስክ መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ከአዲሱ የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ራይዘንኮቭ ጋር መወያየታቸውን እና በሹመታቸውምእንኳን ደስ ያለህ ! ማለታቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሁለቱ ባለስልጣናት በስልክ ባደረጉት ውይይት በአለም አቀፍ እና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን መግለጫው አስነብቧል።
🟠 እስከ ምሽት 11 ሰአት ድረስ በፈረንሳይ በተካሄደው አስቸኳይ የፓርላማ ምርጫ 59.39% ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ተመዝግቧል። ይህ የምርጫ ጣቢያዎቹ ከመዘጋታቸው ከአንድ ሰአት በፊት ያለው አሃዝ መሆኑን የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል።
🟠 የሩሲያ ታጣቂ ሃይሎች በካርኮቭ ከተማ ዳርቻ የሚገኘውን የዩክሬን ብሄራዊ ሻለቃ የክራከን ጦር ሰፈርን መምታቱን በኒኮላይቭ የሚገኘው የሩስያ ሚስጢራዊ አውታር አስተባባሪ ሰርጌ ሌቤዴቭ ለስፑትኒክ ተናግሯል፤
🟠 የየመን አንሳር አላህ ንቅናቄ (ሁቲዎች )በመባል የሚታወቁት ሃይሎች የላይቤሪያ ባንዲራ ባውለበለበችው "ትራንስወርልድ ናቪጌተር "መርከብ ላይ ከሳምንት በፊት ጥቃት መፈጸውን አረጋግጦ፤ራሱ ባሰራው ሰው አልባ ጀልባ ተጠቅሞ ጥቃት ማድረሱን ተናግሯል።
🟠 የኦስትሪያ የፍሪደም ፓርቲ መሪ ኸርበርት ኪክል በአውሮፓ ፓርላማ ከሀንጋሪው ጠቅላይ ሚንስትር ቪክቶር ኦርባን ፊደዝ ፓርቲ እና የቼክ አክሽን ኦፍ ሲትዝን(ANO) ፓርቲ ጋር የፖለቲካ ህብረት መመስረቱን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰኔ 23 ምሽት ዋና ዋና ማጠቃለያ ዜናዎች
የሰኔ 23 ምሽት ዋና ዋና ማጠቃለያ ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 23 ምሽት ዋና ዋና ማጠቃለያ ዜናዎች 🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሞስኮ እና በሚንስክ መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ከአዲሱ የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ራይዘንኮቭ ጋር መወያየታቸውን እና በሹመታቸውምእንኳን... 30.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-30T20:53+0300
2024-06-30T20:53+0300
2024-06-30T21:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий