ደቡብ አፍሪካ፡ የቀድሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ከ30 የሚኒስትሮች ቦታ 6ቱን እንደሚያገኝ ሲነገር፤ ቀሪውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እንደሚይዝ ተነግሯል
ኒውስ 24 የተባለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የዴሞክራቲክ ህብረት ተወካዮች የሚከተሉትን የሚኒስትር ቦታ ይይዛሉ
🟠 ግብርና፣መሬት ሪፎርምና ገጠር ልማት
🟠 መሠረታዊ ትምህርት
🟠 መገናኛ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች
🟠 አካባቢ፣ደን እና አሳ ልማት
🟠 የቤት ጉዳይ
🟠 የህዝብ ስራዎች እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ይመራሉ።
በተጨማሪም የዴሞክራቲክ ሕብረት አባላት፤የገንዘብና ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ውድድር ሚኒስቴር እንዲሁም አዲስ የተቋቋመውን የኢነርጂና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴርን ጨምሮ በድምሩ ስድስት የምክትል ሚኒስትር ቦታዎችን እንደሚይዙ ተነግሯል።
ከ1994-2024 ብቸኛ ገዥ ፓርቲ ሆኖ የቆየው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ በበኩሉ የጸጥታውን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እንዲሁም ሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል።
በአጠቃላይ አዲሱ መንግስት 10 የፓርላማ መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎችን ያካተተ ቢሆንም ፤ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እና ዴሞክራቲስ ሕብረት ብቻ በሚኒስትሮች የስራ መደቦች ላይ ድርድር አድርገዋል ሲል ኒውስ 24 ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ደቡብ አፍሪካ፡ የቀድሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ከ30 የሚኒስትሮች ቦታ 6ቱን እንደሚያገኝ ሲነገር፤ ቀሪውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እንደሚይዝ ተነግሯል
ደቡብ አፍሪካ፡ የቀድሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ከ30 የሚኒስትሮች ቦታ 6ቱን እንደሚያገኝ ሲነገር፤ ቀሪውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እንደሚይዝ ተነግሯል
Sputnik አፍሪካ
ደቡብ አፍሪካ፡ የቀድሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ከ30 የሚኒስትሮች ቦታ 6ቱን እንደሚያገኝ ሲነገር፤ ቀሪውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እንደሚይዝ ተነግሯል ኒውስ 24 የተባለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የዴሞክራቲክ ህብረት ተወካዮች የሚከተሉትን... 30.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-30T20:16+0300
2024-06-30T20:16+0300
2024-06-30T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ደቡብ አፍሪካ፡ የቀድሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ከ30 የሚኒስትሮች ቦታ 6ቱን እንደሚያገኝ ሲነገር፤ ቀሪውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ እንደሚይዝ ተነግሯል
20:16 30.06.2024 (የተሻሻለ: 20:40 30.06.2024)
ሰብስክራይብ