የኮንጎው ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ ከታዋቂውየሩሲያ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አገኙ።

ሰብስክራይብ
የኮንጎው ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ  ከታዋቂውየሩሲያ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አገኙ። በሴንት ፒተርስበርግ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የሩሲያ ከፍተኛ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት ፕሬዝዳንቱን "ለሰብአዊ  ልማት ላበረከቱት አስተዋፅዖ፣ ለአክብሮት እና ለወዳጅነት ምልክት በመሆን " በሚል የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል። ‍በሩሲያ እና በኮንጎ መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማሰብ ፤የዩኒቨርሲቲው የሳይንስ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቱ ንግግር አድርገዋል። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ተልእኮ በቅርቡ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትማለትም በኮንጎ ሪፐብሊክ፣ በካሜሩን ፣ በኢኳቶሪያል ጊኒ እና በኢትዮጵያ ጋር የትብብር ግንኙነት እንደሚያደረግ ይጠበቃል። በዩኒቨርሲቲው እና በእነዚህ ሀገራት መካከል በርካታ የትብብር ስምምነቶችን ለመፈራረም ታቅዷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0