የሰኔ 23 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሰኔ 23 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠የሩሲያ አየር መከላከያ ትናንት ምሽት በኩርስክ፣ ሊፕትስክ፣ ቮሮኔዝ፣ ብራያንስክ፣ ኦርዮል እና ቤልጎሮድ ክልሎች ላይ 36 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጀመሪያው የፕሬዝዳንት ክርክር  ያሳዩትን ደካማ ብቃት ተከትሎ፤የቅርብ ሰዎቻቸው ይቅርብህ ካላሏቸው በስተቀር ከፕሬዝዳንትነት ውድድሩ እንደማይወጡ የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የቅርብ ሰዎች ያሏቸው የባይደን ሚስት ጂል ባይደን፣ ታናሽ እህቱ ቫለሪ፣ አማካሪው ቴድ ካፍማን እና የነጩ ቤተመንግስት አማካሪዎችን ያጠቃልላል ተብሏል። 🟠 በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የተበተነውን የታችኛው ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ መራጮች ዛሬ እሁድ ምርጫ ይካሄዳሉ።ለአውሮፓ ፓርላማ በተካሄደው ምርጫ አብላጫውን ወንበር  በቀኝ ክንፍ ብሄራዊ ፓርቲ መበለጡን ተከትሎ ነው። 🟠በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት በደረሰ ተከታታይ ፍንዳታ በትንሹ 18 ሰዎች ሲሞቱ 48 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን፤የቦርኖ ግዛት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ። 🟠የቱርክ ብሄራዊ መረጃ ድርጅት ዳይሬክተር ኢብራሂም ካሊን ከሃማስ የፖሊት ቢሮ ሃላፊ ኢስማኢል ሃኒዬህ ጋር መወያየታቸውን የቱርክ ሚዲያዎች ዘግበዋል።በዘገባው መሠረት ከእስራኤል ጋር ዘላቂ የተኩስ አቁምን ለማድረግ፣ ታጋቾችን ለመለዋወጥ እና ሰብአዊ እርዳታን ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማድረስ በሚወሰዱ ርምጃዎች ላይ መወያየታቸው ተነግሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0