የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለማስቆም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ፈቀደ

ሰብስክራይብ
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለማስቆም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ፈቀደ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖሊሶችን ያጨናነቁትን ፀረ-ታክስ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ወታደራዊ ሃይል እንዲሰማራ አፅድቋል፣ በአመፁ የሰው በህይወት መጥፋቱን እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ጠተቅሷል።ይህ ውሳኔ የኬንያ የህግ ማህበር (LSK) ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ የፀደቀ ሲሆን ዝርዝር ጉዳዮች በሁለት ቀናት ውስጥ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የመከላከያ ሚኒስቴር የካቢኔ ፀሐፊ አደን ዱአሌ ወታደራዊ ሃይል መሰማራቱን ባለፈው ማክሰኞ ማሳወቁን ተከትሎ ነው። ዱአሌ ድርጊቱን በአመጽ ተቃውሞ ለተፈጠረው የጸጥታ ችግር ፈጣን ምላሽ ለመስጠትያለመ መሆኑን ገልጸዋል። "ሰላምን እና የህዝብን ደህንነት እንጠብቃለን እንዲሁም የሶስቱን የመንግስት ተቋማት ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን እንጠብቃለን" ብለዋል። ነገር ግን የኬንያ የህግ ማኅበር (LSK)ጠበቃ ክሪሶስቶም ዣቪየር አካሃቢ፣ ዱአሌ ወታደራዊ ሃይሎችን ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በአስቸኳይ ለማሰማራት የሰጠው ምክንያት በዝርዝር  አላቀረበም በማለት ወታደራዊ ሃይል የማሰማራቱን ሂደቱን ተችተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0