በቡርኪናፋሶ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ግድግዳ ላይ የሞተር ዘይት እያፈሰሱ "ፈረንሳይ ትውጣ! "የሚል ተቃውሞ አሰምተዋል።

ሰብስክራይብ
በቡርኪናፋሶ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ግድግዳ ላይ የሞተር ዘይት እያፈሰሱ "ፈረንሳይ ትውጣ! "የሚል ተቃውሞ አሰምተዋል። ሰኔ 28 ተቃዋሚዎች በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ ተሰብስበው፤ ከፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት በአስር ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘውን የፈረንሳይ ኤምባሲ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወር ጠይቀዋል። የቡርኪናፋሶ የጥቁር አፍሪካ መከላከያ ሊግ ኃላፊ አብዱል ራስማኔ እንደገለፁት ይህ “ሰላማዊ ሰልፍ” የፈረንሳይ ኤምባሲ ለፕሬዝዳነቱ ቤተ መንግስት ባለው ቅርበት የተነሳ ዜጎች ያላቸውን ስጋት ለመግለጽ ያለመ ነው ብለዋል። ቀደም ሲል የዜጎችዎች ማኅበራት ብሔራዊ አስተባባሪ ለፈረንሳይ ኤምባሲ በዋና ከተማው ወደሚገኙ ሌሎች ቦታዎች እንዲዛወር የአንድ ወር ጊዜ ቢሰጥም ኤምባሲው ምላሽ አልሰጠም። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0