በኢራን በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፤ የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች ክፍት ሆኑ።

ሰብስክራይብ
በኢራን በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፤ የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች ክፍት ሆኑ። የኢራን ባለስልጣናት በህገ መንግስቱ መሠረት ፕሬዝደንቱ ሲሞት አልያም ከአቅም ማነስ ጋር በተገናኘ ተግባሩን መከወን ሳይችል ሲቀር በ50 ቀናት ውስጥ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት በሚያዘው መሠረት፤ ኢራን በአጭር ጊዜ ምርጫ እያካሄደች ነው። ከራይሲ ሞት በኋላ ሀላፊነቱ ለተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ ሞክበር መተላለፉ ይታወሳል። በምርጫው ላይ ያሉት አራቱ እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ፤የለውጥ አራማጁ የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ማሱድ ፔዜሽኪያን እና ሶስት ወግ አጥባቂዎችን ግለሰቦች ለውድድር ቀረበዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሁለተኛ ዙር ድምጽ እ.አ.አ ሐምሌ 5 ይሰጣል። እ.ኤ.አ ግንቦት  19 ራይሲ ከጎረቤት አዘርባጃን ጉብኝት ወደ ኢራን ሲመለሱ ሄሊኮፕተራቸው ተከስክሶ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።ይፋዊ የኢራን ምርመራ የመጀመሪያ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት ሄሊኮፕተሯ በጭጋጋማ አየር ሳቢያ ከኮረብታ ጋር ከተላተመች በኋላ በእሳት መያያዟን ገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0