የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጥቁር ባህር አካባቢ የሚያደርጉት ቅኝት መብዛት ኔቶ እና ሩሲያ በቀጥታ ወደ ግጭት እንዲመሩ ሊያደርግ እንደሚችል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጥቁር ባህር አካባቢ የሚያደርጉት ቅኝት መብዛት ኔቶ እና ሩሲያ በቀጥታ ወደ ግጭት እንዲመሩ ሊያደርግ እንደሚችል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሩስያ መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ የአሜሪካ ስትራቴጂክ ድሮኖች በጥቁር ባህር ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መጨመራቸውን ተከትሎ፤ አሜሪካ ለምታደርገው ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ምላሽ የሚሰጥ ሃሳብ እንዲሰጡ ለጄኔራሎታቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚቀርቡትን የጦር መሳሪያዎች ኢላማ ለማድረግ የስለላ ስራ እያካሄዱ ነው ሲል መግለጫው አስነብቧል። ይህም የአሜሪካ እና የኔቶ አባል ሀገራት በዩክሬን ግጭት ከኪየቭ አገዛዝ ጎን በመሆን የሚያደርጉት ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል ብሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0