በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ጦር የሎጅስቲክስ ማዕከል ላይ በደረሰ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወታደሮች ቁጥር 20 ደርሷል።

ሰብስክራይብ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ጦር የሎጅስቲክስ ማዕከል ላይ በደረሰ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወታደሮች ቁጥር 20 ደርሷል። የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት 2 የቴክኒክ መረጃ ካፒቴኖች እና አንድ ኮማንደር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አማፂ ኤም 23 ንቅናቄ ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት መቁሰላቸውን ቀደም ሲል የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙሃን ቢዝነስ ዴይ ዘግቦ ነበር። “የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ግዛት በሚገኘው ሳኬ በሚገኘው የጦር ሰፈራቸው ላይ በደረሰ የሞርታር ጥቃት የሁለት ወታደሮች ሞት እና ሌሎች 20 ወታደሮች ላይ ደግሞ በደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል።" ማለታቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።  ራማፎሳ ወታደሮቹ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ሲሉ መስዋዕትነት ከፍለዋል ያሉ ሲሆን ፤ ለአደጋው ሰለባዎች እና ቤተሰቦች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች በአካባቢው ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት እንዲሰፍን የባለስልጣናትን ጥረት ለማገዝ በሚል ተሰማርተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0