ሰኔ 20 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
ሰኔ 20 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የተቃዋሚ ፓርቲ  ዲሞክራቲክ አሊያንስ አመራሮች የብሄራዊ አንድነት መንግስት ምስረታን አደጋ ላይ ጥለዋል ሲሉ መክሰሳቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 በምዕራብ ኬንያ በምትገኝ ሆማ ቤይ ከተማ ቢያንስ 11 ሰዎች መቁሰላቸውን ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል። የተወሰኑ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት መቁሰላቸው ተዘግቧል። 🟠 በቦሊቪያ የህግ አስከባሪ አካላት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል ያሏቸው ቢያንስ 10 ወታደራዊ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቦሊቪያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ካርሎስ ዴል ካስቲሎ ዴል ካርፒዮ ሪፖርት አድርገዋል። 🟠 23 ህጻናትን ጨምሮ 66 ሰዎች በሩሲያ ሴቫስቶፖል ከተማ በተፈፀመ ጥቃት ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን የሩሲያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የአውሮፓ ህብረት እና ዩክሬን የጋራ የደህንነት ቃል ኪዳኖችን ተፈራርመዋል። 🟠 የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በዩክሬን ግጭት ዙሪያ ሩሲያን ያላሳተፈ የሰላም ሃሳብ ውጤት አያመጣም ብለዋል። 🟠 ኔቶ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ እና በቤላሩስ ድንበር  ለመከላከያ መስመር ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደማይቃወም ዋና ጸሃፊ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል ። 🟠 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ፤ባርዴላ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን መላክ አይችሉም ሲሉ ማሪን ለፔን ለ ቴሌግራም ጋዜጣ ገልፀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0