ናሚቢያ የድርቅን ተፅእኖ ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክት ልትጀምር ነው።

ሰብስክራይብ
ናሚቢያ የድርቅን ተፅእኖ ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክት ልትጀምር ነው። ናሚቢያ እ.አ.አ በጥር ወር 2025 ሁለተኛውን የውሃ ማጣሪያ ፋብሪካ መገንባት እንደምትጀምር የግብርና ሚኒስትሩ ካሌ ሽሌትትዌን አስታውቀዋል። ከመቶ አመት ወዲህ ባጋጠማት አስከፊ ድርቅ የተጎዳችው ሀገሪቱ እ.አ.አ በ1998 እንዲሰራ እቅድ ተይዞ የነበረውን ፕሮጀክት ግንባታ አፅድቃለች።ማጣሪያው ከ20 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን እ.አ.አ በ2027 መጀመሪያ ላይ ወደ ስራ ይገባል ተብሏል። በአለም ሶስተኛዋ የዩራኒየም አምራች የሆነችው ናሚቢያ የዩራኒየም ዘርፍ ፍለጋ በመስፋፋቱ ሳቢያ የውሃ ፍላጎቷ እየጨመረ መጥቷል። "የእኛ ትልቁ የእድገት ዕቅዶች፣ የማዕድን ስራዎች ማስፋፋት፣ የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችን ማሟላት፣ ግብርና እና የምግብ ምርቶች አቅርቦትን ማሳደግ ነው" ሲሉ ሽሌትዌይን ተናግሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0