ደቡብ አፍሪካ የአውራሪስ አደንን ለመግታት በማሰብ የመጀመሪያውን ራዲዮአክቲቭ ተግባር ላይ አዋለች

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ የአውራሪስ አደንን ለመግታት በማሰብ የመጀመሪያውን ራዲዮአክቲቭ ተግባር ላይ አዋለች የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች አደንን ለመግታት በተደረገው ቀዳሚ ፕሮጀክት በድንበር አካባቢዎች ላይ በቀላሉ እንዲለዩ ለማድረግ እንዲቻል ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሮችን በአውራሪስ ቀንዶች ውስጥ ገጥመዋል። ተግባሩን የመሩት የዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የጨረር እና የጤና ፊዚክስ ክፍል ዳይሬክተር ጄምስ ላርኪን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት፤ “ሁለት ትናንሽ ራዲዮአክቲቭ ቺፖችን በቀንዱ ውስጥ እንዳስቀመጡ ተናግረዋል። የራዲዮአክቲቭ ቁሱ"ቀንዱን ከጥቅም ውጭ ከማድረጉ በተጨማሪ ንጥረ ነገሩ በመሠረታዊነት ለሰው ልጅ ፍጆታ መርዛማ ነው" ሲሉ የዚሁ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፕሮፌሰር ኒታያ ቼቲ አክለዋል። የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር መጠኑ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ በምንም መልኩ የእንስሳትን ጤና እና አካባቢን አይጎዳውም ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ በአለም ላይ ብዙ ቁጥር ያለው አውራሪስ መገኛ መሆኗን ተከትሎ፤ ለቀንዱ ሲባል አውራሪስ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታደንባት ሀገር ናት። የአውራሪስ ቀንድ በተለይ በኤስያ  አህጉር  ለባህላዊ መድኃኒት አገልግሎት ስለሚውል ደቡብ አፍሪካ ዋና የአደን የማደኛ ቦታ ሆና ታገለግላለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0