ሩሲያ ለማሊ ከምታቀርባቸው አጠቃላይ ምርቶች ውስጥ የስንዴ ምርት 40 በመቶ ያህሉን እንደሚሸፍን የማሊ ንግድ ሚኒስትር ተናገሩ።

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለማሊ ከምታቀርባቸው  አጠቃላይ ምርቶች ውስጥ የስንዴ ምርት 40 በመቶ ያህሉን እንደሚሸፍን የማሊ ንግድ ሚኒስትር ተናገሩ። "ከነዳጅ እና ማዳበሪያ በተጨማሪ ማሊ በዋናነት ከሩሲያ የሚገቡ እንደ ስንዴ ያሉ የግብርና ምርቶችን 40 በመቶ ያህል እንደሚጠጋ" የኢንዱስትሪ እና የንግድ ሚኒስትሩ ሙሳ አላሳኔ ዲያሎ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ማሊ የግብርና ምርቶቹን ወደ ሩሲያ ለመላክ እንዳሰበች ጠቁመው ሚኒስቴሩ በዚህ በኩል አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ጠቁመዋል። "ማሊ ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ ካሺው እና ማንጎ ጨምሮ በርካታ የግብርና ምርቶችን ወደ ሩሲያ ለመላክ ብዙ ስራዎችን እየሠራች"መሆኗን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ በተጨማሪም በአፍሪካዊቷ ሀገር የወርቅ ማዕድን ለማውጣት ከሩሲያ ጋራ ተጨማሪ ድርድር እንደሚያስፈልግ እና ከሞስኮ ጋር "የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መፍትሔዎችን" ይጠይቃል ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0