በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል።
የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የሀገሪቱ የዜና ወኪል እንደዘገበው በታሲያ መንደር አቅራቢያ “ በታጠቁ የአሸባሪ ቡድኖች ጥምረት” በፀጥታ ሃይሎች ላይ ባደረሰው ጥቃት 20 ወታደሮች እና አንድ ግለሰብ ፣ በድምሩ 21 ሰዎች ተገድለዋል።
በጥቃቱ ዘጠኝ ወታደሮች መቁሰላቸውን እና በሁለት የሰራዊቱ መኪኖች ላይ ጉዳት መድረሱን መግለጫው ገልጿል።
በሪፖርቱ መሰረት ተሽከርካሪዎቹ እና የመገናኛ መሳሪያዎቹ ሲወድሙ፣12 የሚሆኑ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ተገድለዋል። በተጨማሪም የአየር እና የመሬት አሰሳ በማጠናከር የቀሩትን የአሸባሪው ቡድን አባላት ለማጥፋት ተሰማርተዋል።
የኒዠር ባለስልጣናት ከረቡዕ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሀዘን አውጀዋል፣ በዚህ ጊዜ የሞቱ ወታደሮችን በማስታወስ የሀገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲሰቀል ይደረጋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል።
በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል።
Sputnik አፍሪካ
በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል። የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የሀገሪቱ የዜና ወኪል እንደዘገበው በታሲያ መንደር አቅራቢያ “ በታጠቁ የአሸባሪ ቡድኖች ጥምረት” በፀጥታ... 27.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-27T14:04+0300
2024-06-27T14:04+0300
2024-06-27T14:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል።
14:04 27.06.2024 (የተሻሻለ: 14:40 27.06.2024)
ሰብስክራይብ