በአለም ትልቁ የዱር እንስሳት ፍልሰት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ድኩላዎችን እንደሚያካትት በደቡብ ሱዳን የተካሄደ ጥናት አመላከተ።
ታላቁ የናይል ፍልሰት ተብሎ የሚጠራው አስደናቂ የተፈጥሮ ሁነት ሲሆን፤የቦማ ባዲንጊሎ ጆንግሌይ የመሬት ገጽታ የአየር ላይ ዳሰሳ በደቡብ ሱዳን መንግስት እና መንግሥታዊ ተቋም ባልሆነው የአፍሪካ ፓርኮች መካከል እየተደረገ ያለው ትብብር አካል ሲሆን አካባቢውን ለትውልድ ጠብቆ ማስተላለፍን ዓላማ ያደረገ ነው።
"በደቡብ ሱዳን እየቀጠለ ያለውን እድገት ለማፋጠን፤ የዱር እንስሳትን ዘርፍ ወደ ዘላቂ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለመቀየር ቁርጠኞች ነን። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የጸጥታ ሀይሎች በተለይም የዱር እንስሳት ሚኒስቴር እና አጋሮቹ ጥበቃ በሚደረግላቸው አካባቢዎች ህገ-ወጥ የዱር እንስሳትን አደን እና ዝውውርን ለመከላከል የዱር እንስሳትን መጠለያ ሠራተኞችን በማሰልጠን እና በቂ ቁሳቁሶችን ማሟላት ላይ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ሲሉ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን ተናግረዋል።
ጥናቱ 122,774 ኪ.ሜ.ስኬዌር የሚሸፍን ሲሆን አጠቃላይ የታላቁ የናይል ፍልሰት አራቱን ዋና አንቴሎፕ ዝርያዎችያሉባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ፤ከደቡብ ሱዳን እስከ ኢትዮጵያ ያለውን አካባቢ የስነ-ምህዳር ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ለማሳየት ከ 251 የክትትል ኮላሎች በትላልቅ አጥቢ እንስሳት ላይ ያለውን መረጃ ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በአለም ትልቁ የዱር እንስሳት ፍልሰት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ድኩላዎችን እንደሚያካትት በደቡብ ሱዳን የተካሄደ ጥናት አመላከተ።
በአለም ትልቁ የዱር እንስሳት ፍልሰት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ድኩላዎችን እንደሚያካትት በደቡብ ሱዳን የተካሄደ ጥናት አመላከተ።
Sputnik አፍሪካ
በአለም ትልቁ የዱር እንስሳት ፍልሰት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ድኩላዎችን እንደሚያካትት በደቡብ ሱዳን የተካሄደ ጥናት አመላከተ። ታላቁ የናይል ፍልሰት ተብሎ የሚጠራው አስደናቂ የተፈጥሮ ሁነት ሲሆን፤የቦማ ባዲንጊሎ ጆንግሌይ የመሬት ገጽታ የአየር ላይ ዳሰሳ... 27.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-27T12:13+0300
2024-06-27T12:13+0300
2024-06-27T12:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በአለም ትልቁ የዱር እንስሳት ፍልሰት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ድኩላዎችን እንደሚያካትት በደቡብ ሱዳን የተካሄደ ጥናት አመላከተ።
12:13 27.06.2024 (የተሻሻለ: 12:40 27.06.2024)
ሰብስክራይብ