የሰኔ 19 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች፡-
🟠 በኬንያ የታክስ ጭማሪ የተቃወሞ ሰልፍ 22 ሰዎች እንደሞቱ የሀገር ውስጥ የህክምና ባለሙያዎችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኬንያ ፕሬዝዳንት በድምሩ 6 ወጣቶች ህይወታቸዉን ማጣታቸውን እና ህዝባዊ አመፁን የቀሰቀሰው የበጀት ረቂቅ ህግ እንደማይፀድቅ አስታውቀዋል። አወዛጋቢው ሰነድ እንደገና እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ ይላካል ተብሏል፣
🟠 ሩሲያ ከኬንያ እና ቻድ ጋር ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነቷን ለማጎልበት ከቪዛ ነፃ ጉዞ ለመጀመር እየተነጋገረች እንደሆነ በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ የሩሲያ ኤምባሲዎች ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፣
🟠 ጁሊያን አሳንጅ ካንቤራ ሲደርስ ለጋዜጠኞች ቃል አልሰጠም። ሚስቱ ነገሮች ሲስተካከሉ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግራለች፣
🟠 የዩክሬን ሃይሎች በካኮቭካ የውኃ ማጠራቀሚያ ዳርቻ በሲቪል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠሩ የድሮን ጥቃታቸውን ጨምረዋል። የዛፖርዥያ ክልል ባለስልጣናት በኢነርጎዳር የጨረር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይካሄዱ እንደነበር ሪፖርት አድርገዋል፣
🟠 ሩሲያ ከጆርጂያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ወደነበረበት ለመመለስ ዝግጁ እንደሆነች እና በዚህ ጉዳይ ከቲብሊሲ የሚመጡ ተነሳሽነቶችን እንደምትደግፍ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል፣
🟠 አንዳንድ የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፣
🟠 የኔቶ ዋና ጸሃፊ ተተኪያቸው ሩተን ተቀብለዋል። ዋና ጸሃፊው ስቶልተንበርግ ኔቶን "በጥሩ እጅ" ላይ
ጥዬ ነው የምለቀው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰኔ 19 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች፡-
የሰኔ 19 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የሰኔ 19 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች፡- 🟠 በኬንያ የታክስ ጭማሪ የተቃወሞ ሰልፍ 22 ሰዎች እንደሞቱ የሀገር ውስጥ የህክምና ባለሙያዎችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኬንያ ፕሬዝዳንት በድምሩ 6 ወጣቶች ህይወታቸዉን ማጣታቸውን እና ህዝባዊ... 26.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-26T21:24+0300
2024-06-26T21:24+0300
2024-06-26T21:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий